እግዚአብሔር ከምትለምነውም ከምታስበውም በላይ ሊያደርግ ይችላል

ምንም ኃይል እንደሌለህ ነገር ግን ልዩነት ልታመጣ እንደምትችል ተሰምቶህ ያውቃል?

ነኅምያን ተመልከት ምንም ገንዘብ አልነበረውም፣ ምንም ስልጣን አልነበረውም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ታሪክን ለመለወጥ ተጠቀመበት፡፡

ነኅምያ ለንጉስ አርጤክስስ ጠጅ አሳላፊ ሆኖ ያገለግል ነበር፡፡ የማይመቻመቸው ታማኝነቱ እና ታማኝ አገልግሎቱ የንጉሱን አመኔታ እንዲያገኝ አድርጎታል፡፡

ወንድሞቹ በኢየሩሳሌም የነበረውን ስደት መጥተው በነገሩት ጊዜ ተቀምጦ አልቅሷል፡፡ የነገሩትም፡ “እነርሱም በዚያ ስፍራ ያሉት ከምርኮ የተረፉት ቅሬታዎች በታላቅ መከራ እና ስድብ አሉ፤ የኢየሩሳሌምም ቅጥር ፈርሷል፡፡ በሮችዋም በእሳት ተቃጥለዋል፡ አሉኝ፡፡” ነኅ 1፡3

ነኅምያ ለእስራኤል ሕዝቦችና ለኢየሩሳሌም ከተማ እጅግ ግድ ይለው ነበር፡፡ ዜናውን በሰማ ጊዜ በአእምሮው ምን እንደሚያስፈልግ አየ፣ ህመሙ በልቡ ተሰማው፣ እናም ይህ ወደ ጸሎት መራው፡፡

እንደዚህ ያስባል ብለን መገመት እንችላለን፡ “ይህን በሚመለከት በተግባር ምን ማድረግ እችላለሁ? እኔ ለንጉሱ ጠጅ የማሳልፍ አንድ ሰው ነኝ፡፡” 

ውድ አንባቢ፡ ምንም ኃይል እንደሌለህ ነገር ግን ልዩነት ልታመጣ እንደምትችል ተሰምቶህ ያውቃል፡፡

ነኅምያም የተሰማው ልክ እንደዚህ ነበር፡፡ ነገር ግን ምንም እንኳን ኃይል ባይኖረውም ሁሉን ወደሚችለው አምላክ ፊቱን መልሶ ነበር፡፡

በሚቀጥለው ሳምንት፡- እግዚአብሔር ቅጥርን ለመስራትና የከተማን ደኅንነት ለመመለስ የተጠቀመበትን የአንድ ጠጅ አሳላፊ አስደናቂ ታሪክ እንከፋፈላለን፡፡

ደካማነትንህ እንድታሸንፍና በእርሱ እንድትታመን እግዚአብሔርን በድፍረት ጠይቀው፡፡

ዌስ እና ጆይ፡

 “ይህ የራእይ ኃይል፡ እግዚአብሔር ለሕይወትህ ያለውን ራእይ ማወቅ፡፡” በሚለው ትምህርት አራተኛው ክፍል ነው፡፡ እነዚህ ተከታታይ ትምህርቶች የተዘጋጁት እግዚአብሔር ለሕይወትህ ያለውን ታላቅ አላማ እንድትረዳ ነው፡፡

Vision

To see an indigenous discipled churches in every unreached villages of Ethiopia.

Address

Church Multiplication Gospel Mission Ministry

Mekanisa area in front of Taxi Station MYPPIC Building 

Office Number 307 

P.O.Box: 40243, Addis Ababa, Ethiopia

Contact Info

Mobile: +251 91 162 1558

Phone: +251 11 844 3860

Email: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.