የመሳርያ ሳጥን ውስጥ ምን አለ?

እያንዳንዱ ሰው ወንድ ወይም ሴት ስራቸውን ለመስራት የሚያስፈልጋቸውን መሳርያዎች እና ቁሳቁሶች ልዩ ሳጥን አላቸው፡፡

እያንዳንዱ ስራ የተለያዩ አይነት መሳሪያዎችን ይጠይቃል የቧንቧ ሰራተኞች የኤሌክትሪክ ወይንም የመካኒክ መሳሪያዎችን አይጠቁሙም፡፡ እንዲሁም በተገቢው መሳሪያዎች ተገቢውን ስራ እንደመስራት ያለሙያዊ ስራ የለም፡፡ ወይም በተሳሳተ መሳሪያ የተሳሳተ ስራ እንደመስራት ያለ የከፋ ሙያዊ ያልሆነ ስራ እንደመስራት ያለ ኪሳራ የለም፡፡

መንፈሳዊ የመሳሪያ ሳጥን

ጥሪያችሁ ለሰባኪ፣ ለማህበራዊ ሰራተኛ፣ የንግድ፣ ስራ ፈጣሪ ወይም በቀላሉ በስራህ ቦታ የክርስቶስ ምስክር ለመሆን ይችላል፡፡ እግዚአብሔር ስራህን እንድታከናውን እነዚን መንፈሳዊ የመሳሪያ ሳጥን አስፈላጊውን መሳሪያዎች ሳያቀርብ አይተውህም ፍቃደኛ ከሆንክ፡፡ 

እንደ መፅሐፍ ቅዱስ መሪዎች ስራችን መንፈሳዊ ነው፡፡ በዓለማዊ የሥራ ቦታ ውስጥ እንኳን ቢሆን ከሰዋዊ ችሎታችን ባሻገር የእግዚአብሔር መንፈስ ደግሞ ለተወደዱ ሰዎች ራዕያቸውን ያሳኩ ዘንድ ለየት ያለ መለኮታዊ ስጦታዎችን አዘጋጅቶል፡፡

መፅሐፍ ቅዱስ እነዚን ስጦታዎች የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች (መንፈሳዊ ስጦታዎች) በማለት የሚጠራቸው ናቸው፡፡

እነዚህም፡- መንፈስ ቅዱስ ለቤተ ክርስቲያን አባላት የሚያከፋፍለው ልዩና መለኮታዊ ባህሪያት በቤተ ከልርስቲያን ውስጥ ለማገልገል እና በዓለም ውስጥ ወንጌልን ለማወጅ የሚያስችሉ ልዩ ልዩ ስጦታዎችን ለግለሰብ አማኞች በአደራ ሰጥቷል እንደ መፅሐፍ ቅዱስ ባለራዕይ መሪዎች በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ የምንሰራው ስራ አለ፡፡ ለዚህም ተገቢውን የመሳሪያ ሳጥን እንፈልጋለን አንድ ታላቅ መንፈሳዊ መሳሪያ ሳጥን ለማዘጋጀት የሚረዱ ሶስት እርምጃዎች እነሆ፡-

ስጦታዎን ይወቁ

እያንዳንዱ ክርስቲያን የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ ነው፡፡ ይህ ማለት ምን ማለት ነው? እየአንድ አንዱ ስጦታ ለእየአንድ አንዱ ክርስቲያን አለ ማለት ነው፡፡ ሆኖም መፅሐፍ ቅዱስ እነዚህ ስጦታዎችን ለቤተ ክርስቲያን ይሰጣቸዋል ይህም የሚያመለክተው ሁሉም ስጦታ ያለው አማኝ የለም እየአንድ አንዱ አማኝ በአደራ የተሰጠውን ስጦታ የማወቅ እና የመለየት አላፊነት አለበት፡፡ እንዴት ይህን ማድረግ እንደምትችል እነሆ፡-

  • ቅዱስ ቃሉን አጥና ፡- የመሳሪያው ሳጥን ምን እንደሚመስል እና በውስጥ ምን መሳሪያዎች እንዳሉ ለመለየት በዋናነት የሚረዳህ መፅሀፍ ቅዱስ ነው፡፡ 
  • ሕይወትህን መርምር፡- እግዚአብሔር ለክብሩ አንተን የሚጠቀምባቸውን የተወሰኑ ቦታዎችን ለይ ከነዚ ስጦታች መካከል አንድ አንዶቹ ለቤተ ክርስቲያን እና ለመላው ዓለም ተገልጠው ይሆናል፡፡
  • ጥሩ ምክር ፈልግ፡- የበሰሉ መሪዎችን አዋራ እነዚ ሰዎች እያሰብክ ያለውን ሊያረጋግጡልህ፣ እስካሁን ያላየኸውን ፀጋ ሊለዩልህ ወይም በመንፈስ ሳይሆን በስጋ እያገለገልክበት ባለው ነገር ላይ ሊያርሙክ ይችላሉ፡፡

ስጦታዎችህን አዳብር

እንደ መንፈሳዊ ስጦታዎች ባለ አደራ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን ለመጠቀም ችሎታዎችህን የማዳበር ሐላፊነት አለብህ፡፡

እየአንድ አንዱ አማኝ ስጦታዎቻቸውን የመለየት እና በላቀ እውቀትና ተግባራዊ ልምምዶች ችሎታቸውን ለመጠቀም ማደግ አለባው፡፡ ልታደርጋቸው የሚገቡ ጥቂት ነገሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡

  • ከስጦታዎችህ ጋር የሚገናኙ የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍሎችን አጥና
  • ተጨማሪ መፅሐፍትን አንብብ፡፡ በዚ ጉዳይ ላይ ከተለያዩ ባህሎች የሆኑ የመፅሐፍት ሐብቶች አሉ፡፡

Vision

To see an indigenous discipled churches in every unreached villages of Ethiopia.

Address

Church Multiplication Gospel Mission Ministry

Mekanisa area in front of Taxi Station MYPPIC Building 

Office Number 307 

P.O.Box: 40243, Addis Ababa, Ethiopia

Contact Info

Mobile: +251 91 162 1558

Phone: +251 11 844 3860

Email: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.